ቀጥታ፡

አየር መንገዱ ለቀድሞ የኩባንያው መሪዎች ዕውቅና ሰጠ

አዲስ አበባ፤ ጥር 10/2017(ኢዜአ):- የኢትዮጵያ አየር መንገድ አየር መንገዱን በሥራ አስኪያጅነት እና በዋና ሥራ አስፈጻሚነት ለመሩ የቀድሞ የኩባንያው መሪዎች የዕውቅና እና ሽልማት ሰጥቷል።

በዚህም ኮሎኔል ስምረት መድሀኔ፣ ካፒቴን ዘለቀ ደምሴ፣ አህመድ ኬሎ(ዶ/ር)፣ አቶ ብስራት ንጋቱ፣ አቶ ግርማ ዋቄ እና አቶ ተወልደ ገብረማርያም አየር መንገዱ ዛሬ ለደረሰበት ስኬት እና ዓለም አቀፍ ዝና ላበረከቱት የማይተካ የመሪነት አስተዋፅጾ ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል።

ብሔራዊ ኩራት የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ78 ዓመት በላይ በበርካታ ደማቅ ስኬቶች ታጅቦ ዛሬ ላይ ደርሷል።

የአየር መንገዱ በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ውስጥ የያዘውን ጉልህ ስፍራ እና ያልተቋረጠ የስኬት ጉዞ በትውልድ ቅብብሎሽ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም