ጥምቀትን በልዩ ድምቀት በምታስተናግደው ጎንደር የከተራ ክዋኔ - ኢዜአ አማርኛ
ጥምቀትን በልዩ ድምቀት በምታስተናግደው ጎንደር የከተራ ክዋኔ
አዲስ አበባ፤ ጥር 10/2017(ኢዜአ)፦ ከተራ በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ በድምቀት መከበር ጀምሯል።
በአሁኑ ሰዓት የበርካታ አድባራት ታቦታት ከመንበረ ክብራቸው ወጥተው በካህናት፣ በሰንበት ተማሪዎችና በበዓሉ ተሳታፊዎች ዝማሬና እልልታ ታጅበው ወደ ባህረ ጥምቀቱ እየተጓዙ ይገኛሉ።
በክብረ በዓሉ ላይ ለመሳተፍ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና ከተለያዩ ክፍለ ዓለማት የመጡ ገብኝዎች ጎንደር ከትመዋል።
ጥምቀትን በጎንደር ለማክበር እንግዶች ከቀናት በፊት ጀምሮ ወደ ከተማዋ እየገቡ ሲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዛሬው ዕለትም በርካታ የበዓሉ ተሳታፊዎችን እያጓጓዘ ነው።
የጎንደር ከተማ የኮሪደር ልማት እና የአፄ ፋሲል ግንብ እድሳት በዓሉን ውብ ገጽታ አላብሰውታል።