ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ እና ብራዚል በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን መስክ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገለጹ

አዲስ አበባ፤ ጥር 9/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና ብራዚል በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን መስክ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ለማጎልበት እንደሚሰሩ አስታወቁ።

በብራዚል የኢትዮጵያ አምባሳደር ልዑልሰገድ ታደሰ ከብራዚል የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ሚኒስቴር የሁለትዮሽ ትብብር ዋና አስተባባሪ ቫኒያ ጎሜዝ ዳ ሲልቫ ጋር ተወያይተዋል።

አምባሳደሩ በውይይቱ ኢትዮጵያ እና ብራዚል በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን መስክ የተፈራረሙትን ስምምነት ትግበራ ለማፋጠን በጋራ ለመስራት ከስምምነት ላይ መደረሱን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

ስምምነቱ በተለይም ሁለቱ ሀገራት በብዝሃ ህይወት፣ በዘላቂ ልማት፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት እና የኢንዱስትሪ ዘርፎች ላይ ያላቸውን ትብብር የሚያጠናክር ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም