ቀጥታ፡

በኢትዮጵያ እና በኢራን ምክር ቤቶች መካከል የተካሄደው ውይይት ውጤታማ እና የሁለቱን ሀገሮች ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የበለጠ የሚያጠናክር ነው - አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ

አዲስ አበባ፤ ጥር 9/2017(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ እና በኢራን ምክር ቤቶች መካከል የተካሄደው ውይይት ውጤታማ እና የሁለቱን ሀገሮች ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የበለጠ የሚያጠናክር ነው ሲሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ገልጸዋል።

አቶ ታገሰ ጫፎ በኢራን ሪፐብሊክ መንግስት ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ዶክተር መሐመድ ጋሊባፍ የሚመራውን ልዑክ በቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተገኝተው አሸኛኘት አድርገዋል።


 

በኢትዮጵያና በኢራን ምክር ቤቶች መካከል የተካሄደው ውይይት ውጤታማ እና የሁለቱን ሀገሮች ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የበለጠ የሚያጠናክር መሆኑን አፈ-ጉባኤው አስታውቀዋል።

የኢራን ምክር ቤት የልዑክ ቡድን በቆይታው በሁለቱ ሀገራት ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር አድርጓል።

ልዑኩ በኢትዮጵያ ቆይታው ብሔራዊ ቤተመንግስትንና የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየምን መጎብኘቱ እንዲሁም ዶክተር መሐመድ ጋሊባፍ ከአፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ጋር በመሆን በምክር ቤቱ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ማከናወናቸውን የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም