የፌዴራልና የጋምቤላ ክልል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በክልሉ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የፌዴራልና የጋምቤላ ክልል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በክልሉ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው
ጋምቤላ ጥር 09/2017-- የፌዴራልና የጋምቤላ ክልል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በክልሉ የኮሪደር ልማትን ጨምሮ የተለያዩ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው።
በጉብኝቱ ላይ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ፣ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር መሀመድ አብዱረህማን እና ሌሎች የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
የስራ ሀላፊዎቹ ጉብኝታቸው በጋምቤላ ከተማ የተጀመረውን የኮሪደር ልማትና በከተማ አስዳደሩ እየተገነቡ የሚገኙ የመንገድ መሠረተ ልማቶችን ተመልክተዋል።
በቀጣይም በጋምቤላ ክልል በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አየተገነቡ በሚገኙ የመንገድ መሠረተ ልማቶች ዙሪያ ውይይት እንደሚደረግ ይጠበቃል።