ፓርቲው የገባውን ቃል በተግባር በመፈፀም ቃሉን ባህል አድርጎ እየሰራ ይገኛል- አቶ ጌቱ ወዬሳ - ኢዜአ አማርኛ
ፓርቲው የገባውን ቃል በተግባር በመፈፀም ቃሉን ባህል አድርጎ እየሰራ ይገኛል- አቶ ጌቱ ወዬሳ
አዲስ አበባ፤ ጥር 8/2017(ኢዜአ):- የብልፅግና ፓርቲ በመጀመሪያው ጉባዔ የገባውን ቃል በተግባር በመፈፀም ቃሉን ባህል አድርጎ እየሰራ እንደሚገኝ የብልፅግና ፓርቲ የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ ገለፁ።
አቶ ጌቱ ወዬሳ ኮንፍረንሱ መጠናቀቁን ተከትሎ በሰጡት መግለጫ ፓርቲው በአንደኛው ጉባዔው ለህዝብ የባውን ቃል ዕውን በማድረግ በርካታ ስኬቶችን እያስመዘገበ የሚገኝ መሆኑን ገልፀዋል።
የብልፅግና ፓርቲ የልማት ፕሮጀክቶችን በአጭር ግዜ ጀምሮ በጥራት በማከናወን ቀድሞ የነበረውን የስራ ባህል የቀየረ ፓርቲ ነውም ብለዋል።
በተለይ ህብረ ብሄራዊነት እና አንድነትን በማጎልበት በአመራሩ መካከል በተፈጠረው የወንድማማችነት እና እህትማማችነትን መንፈስ የአገሪቱን የፖለቲካና የኢኮኖሚ ስብራቶች በመጠገን ብሎም ማህበራዊ እሴቶችን በማጎልበት አሻጋሪ ፕሮግራሞችን ቀርፆ በመተግበር በሁሉም ዘርፍ ተጨባጭ ድሎችን ማስመዝገብ የቻለ መሆኑን ገልፀዋል።
በክልሉ በተፈጠረው ጠንካራ የስራ ባህል በልማት ስራዎች፤ የመልካም አስተዳደር እና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ እመርታዊ ውጤቶች እየተመዘገቡ እንደሚገኙም ጠቁመዋል።
ሲካሄድ የነበረው የቅድመ ጉባኤ ኮንፍረንስም የአስተሳሰብ እና የተግባር አንድነትን ይበልጥ በማጎልበት ለቀጣይ ተልዕኮ እና ስኬት ለአመራሩ አቅም የተፈጠረበት መሆኑን አክለዋል።
ኮንፈረንሱ በክልሉ ሁሉም የመንግስት ተቋማት እና በወረዳዎች የሚገኙ የመሰረታዊ ድርጅቶች የተሳተፉበት ሲሆን የዲሞክራሲ ባህል እየዳበረ መምጣቱ የታየበት መሆኑንም አቶ ጌቱ ወዬሳ ገልፀዋል።
በክልል ደረጃ በተካሄደው የማጠቃለያ ኮንፍረንስ በቀጣይ በሚካሄደው የብልፅግና ፓርቲ ጉባኤ የሚሳተፉ አባላትን በዲሞክራሲያዊ መንገድ በመምረጥ መጠናቀቁን ገልጸዋል።