የኢራን ፓርላማ ልዑካን ቡድን አባላት ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል - ኢዜአ አማርኛ
የኢራን ፓርላማ ልዑካን ቡድን አባላት ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል
አዲስ አበባ፤ጥር 8/2017(ኢዜአ)፦በኢራን ፓርላማ አፈ ጉባኤ በዶክተር መሐመድ ባቀር ቃሊባፍ የተመራው የልዑካን ቡድን አባላት አዲስ አበባ ገብተዋል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዴኤታ ብርቱካን አያኖ ለልዑካን ቡድኑ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በመገኘት አቀባበል አድርገዋል።
የኢራን ፓርላማ ልዑክ ቡድን አባላት በቆይታቸው የተለያዩ ጉብኝቶችን እንደሚያደርጉና ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ እና ከሌሎች የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ ተገልጿል።