ቀጥታ፡

በቻይና የመንግስት ምክር ቤት የልማት ምርምር ማዕከል ፕሬዝዳንት ሉ ሃኦ የተመራ ልዑክ አዲስ አበባ ገባ

አዲስ አበባ ፤ ጥር 8/2017 (ኢዜአ)፦ በቻይና የመንግስት ምክር ቤት የልማት ምርምር ማዕከል ፕሬዝዳንት ሉ ሃኦ የተመራ የልዑካን ቡድን ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገብቷል።

ልዑኩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ እንዳለው መኮንን አቀባበል አድርገዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ በቆይታው ከንግድና ቀጣናዊ ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ጋር በኢትዮጵያ እና ቻይና የሁለትዮሽ የንግድና ኢንቨስትመንት እንዲሁም ተጓዳኝ ጉዳዮች ላይእንደሚወያይ ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል::

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም