ቀጥታ፡

የተባበሩት መንግስታት የምግብ ስርዓት ጉባዔ በኢትዮጵያ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፤ ጥር 7/2017(ኢዜአ)፦ የተባበሩት መንግስታት የምግብ ስርዓት ጉባዔ (UNFSS+4) በአዲስ አበባ ይደረጋል።

በጣልያን የኢትዮጵያ አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ ከዓለም ምግብ እና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) የዘላቂ ልማት ግቦች ቢሮ ዳይሬክተር ስቴፋኖስ ፎቲዩ ጋር ተወያይተዋል።

ሁለቱ ወገኖች በውይይታቸው ከሐምሌ 21 እስከ 23 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ለሚካሄደው የተባበሩት መንግስታት የምግብ ስርዓት ጉባዔ መደረግ ስላለበት የቅድመ ዝግጅት ስራ ሀሳቦችን ተለዋውጠዋል።


 

ኢትዮጵያ እና ፋኦ ለጉባዔው ዝግጅት ስራ የጋራ ኮሚቴ ለማቋቋም ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።

ፋኦ ከኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ጉባዔውን እንደሚያዘጋጅ በሮም የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

የዘንድሮው የተባበሩት መንግስታት የምግብ ስርዓት ጉባዔ የረጅም ጊዜ ፈተናዎች ምላሽ መስጠት የሚያስችል ጠንካራ የምግብ ስርዓት መገንባት ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም