በለውጡ ዘመን ለኢትዮጵያ ከተሞች ልማት ትልቅ ትኩረት ተሰጥቷል- ከንቲባ አዳነች አቤቤ - ኢዜአ አማርኛ
በለውጡ ዘመን ለኢትዮጵያ ከተሞች ልማት ትልቅ ትኩረት ተሰጥቷል- ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባ፤ ጥር 7/2017(ኢዜአ)፡- በለውጡ ዘመን ለኢትዮጵያ ከተሞች ልማት ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ከንቲባ አዳነች፥ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ከቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ጋር በመሆን የጎንደር የኮሪደር ልማት እና የፋሲለደስ ግንብ እድሳት የደረሰበትን ደረጃ መጎብኘታቸውን ገልጸዋል።
የጎንደር ከተማ የኮሪደር ልማት ስራ እና የፋሲለደስ እድሳት እጅግ በጣም ውብ፣ የከተማዋን ታሪካዊነት ይበልጥ በሚያጎላ እና የቱሪስት መዳረሻነቷን በሚያሳድግ ሁኔታ በመሰራት ላይ ነው ብለዋል።
በለውጡ ዘመን የኢትዮጵያ ከተሞች የተሰጣቸው ትኩረት እጅግ ትልቅ ነው።
ከንቲባዋ በተለይም ከተሞች ለነዋሪዎች ምቹ እና ውብ እንዲሁም የቱሪስት መስህብነታቸውን የሚጨምር ስራ በመከናወን ላይ እንደሚገኝም ነው ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የገለጹት።