ቀጥታ፡

ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ የአዋጭነት ጥናት ሰነድ ተረከበ

አዲስ አበባ፤ ጥር 7/2017(ኢዜአ)፦ የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ የአዋጭነት ጥናት ሠነድን አጠናቆ አስረክቧል።

ለኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ተጠሪ ተቋም የሆነው የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት በጥናትና ማማከር ዘርፍ፤ በአዋጭነት ጥናት፤ በንብረት ትመና እና በተለያዩ የአገልገሎት ዘርፎች ከተለያዩ መንግስት ተቋማት ጋር ላለፉት ዓመታት ሲሰራ የቆየ አንጋፋ ተቋም ነው።

በዚህንም አገልግሎቱ በወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ላይ ያደረገውን የአዋጭነት ጥናት አጠናቆ ዛሬ አስረክቧል።

የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሽፈራው ሰለሞን እና የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጀማል አማን የጥናት ሰነዱን ተረካክበዋል።

አቶ ሽፈራው በዚሁ ወቅት እንደገለፁት የአዋጭነት ጥናት ሰነድ ፋብሪካውን በፍጥነት ወደ ተግባር ገብቶ የሃገር ውስጥ የስኳር ተደራሽነት ሽፋን ከማሳደጉ በተጨማሪ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነት ያግዛል።

የወንጅ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጀማል አማን በበኩላቸው ወንጅ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ እንደ ሃገር በርካታ ስራዎችን የሚሰራ ፋብሪካ መሆኑን ጠቅሰዋል።

አሁን የተረከበው የአዋጭነት ጥናት ሰነድን በአጭር ጊዜ ወደ ትግበራ እንደሚገባ ማረጋገጣቸውን ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ያገነኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም