ኖርዌይ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማሳደግ ቁርጠኛ ናት- የኖርዌይ የፍትህ ሚኒስትር ኤምሊ ኧንገር - ኢዜአ አማርኛ
ኖርዌይ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማሳደግ ቁርጠኛ ናት- የኖርዌይ የፍትህ ሚኒስትር ኤምሊ ኧንገር
አዲስ አበባ፤ጥር 6 / 2017 (ኢዜአ):-ኖርዌይ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማሳደግ ቁርጠኛ ናት ሲሉ የኖርዌይ የፍትህ ሚኒስትር ኤምሊ ኧንገር መኸል ገለጹ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞትዮስ (ዶ/ር)የኖርዌይ ፍትህ ሚኒስትር ኤምሊ ኧንገር መኸል ጋር ዛሬ በፅ/ቤታቸው ተወያይተዋል ።
ሚኒስትሩ በውይይቱ ላይ እንዳሉት፥ ኖርዌይ የኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ አጋር ከሆኑ አገራት መካከል አንዷ ነች።
የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት አሁን ካለበት ደረጃ ይበልጥ ለማጠናከር ኢትዮጵያ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት ገልፀዋል።
በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ በመተግበር ላይ የምትገኘው የኢኮኖሚ ሪፎርም ለውጭ ኩንያዎች የተሻለ የተሳትፎ ዕድልን የፈጠረ በመሆኑ የኖርዌይ ባለሃብቶች መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ አቅርበዋል።
የኖርዌይ ፍትህ ሚኒስትር ኤምሊ ኧንገር መኸል በበኩላቸው፥ ኖርዌይ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንነኙነት ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆኗን መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመለክታል።