ሳምሶን መኮንን (ዶ/ር) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ - ኢዜአ አማርኛ
ሳምሶን መኮንን (ዶ/ር) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፤ ጥር 6 /2017(ኢዜአ)፡-የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሳምሶን መኮንን (ዶ/ር) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር እንዲሆኑ የቀረበለትን ሹመት አፀደቀ።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 15ኛ መደበኛ ጉባዔውን አድርጓል።
ምክር ቤቱ ሳምሶን መኮንን (ዶ/ር) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው እንዲሾሙ የቀረበለትን ጥያቄ አፅድቋል።
አዲሱ ተሿሚ ከዚህ ቀደም የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር የነበሩትን መሐመድ እድሪስ ተክተው ይሰራሉ።
አቶ መሐመድ እድሪስ የሰላም ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው ይታወቃል።
ሳምሶን መኮንን (ዶ/ር) በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ በአስተማሪነት እና በአመራርነት ማገልገላቸው ተገልጿል።
ሹመታቸውም በአብላጫ ድምጽ ፀድቋል።