ቀጥታ፡

የቤንች የዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል "ቢስት ባር" በሚዛን አማን ከተማ እየተከበረ ነው

ሚዛን አማን ፤ ጥር 6/2017(ኢዜአ)፡-የቤንች የዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል "ቢስት ባር" ማጠቃለያ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በተገኙበት በሚዛን አማን ከተማ እየተከበረ ነው።

የቤንች ዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል "ቢስት ባር" በሚዛን አማን ከተማ እየተከበረ ነው።


 

የበኩር ወይም አዲስ የደረሰን እህል በመቅመስና ለፈጣሪ ምስጋና በማቅረብ በሚከበረው ቢስት ባር ልጆችም በአባቶቻቸው ይመረቃሉ።

በሚዛን አማን የቀድሞ አየር ማረፊያ እየተካሄደ ባለው የበዓሉ ማጠቃለያ መርሃ ግብር ላይ የፈረስ ጉግስ ውድድር ትርኢት ቀርቧል።

ለበዓሉ የቤንች ባህላዊ ምግብና መገልገያ ቁሳቁስ አውደርዕይ የተዘጋጀ ሲሆን የአባቶች ምረቃ ሥነ ሥርዓት የበዓሉ አካል መሆኑ ታውቋል።

በበዓሉ ላይ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችም ተገኝተዋል።

ቢስት ባር የተጣሉት ከታረቁ በኋላ የሚከበር የይቅርታ በዓል ነው።

በበዓሉ የመጀመሪያውን እህል ታላላቆች ከቀመሱ በኋላ በዕድሜ ደረጃ ታናሾች እንዲቀምሱ የሚደረግበት እሴትም ጎልቶ ይንጸባረቃል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም