ቀጥታ፡

ምክር ቤቱ መደበኛ ጉባዔውን እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፤ጥር 6 /2017(ኢዜአ)፡- የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 15ኛ መደበኛ ጉባዔውን በማድረግ ላይ ይገኛል።

ምክር ቤቱ በጉባዔው የንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ በፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።

በተጨማሪም የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ሁለት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች ላይ ያቀረበውን የስንብት ውሳኔ አስመልክቶ የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ እንደሚያፀድቅ ተገልጿል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሹመትን መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅም ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም