የብራዚል የአስጎብኚ ድርጅቶች ማህበር የኢትዮጵያን ቱሪዝም ለማስተዋወቅ በትብብር ለመስራት ይሁንታውን ገለፀ - ኢዜአ አማርኛ
የብራዚል የአስጎብኚ ድርጅቶች ማህበር የኢትዮጵያን ቱሪዝም ለማስተዋወቅ በትብብር ለመስራት ይሁንታውን ገለፀ
አዲስ አበባ፤ ጥር 5/2017 (ኢዜአ)፦ ግዙፉ የብራዚል የቱሪስት አስጎብኚ ድርጅቶች ማህበር ኢትዮጵያን እንደ ቱሪስት መዳረሻ በማስተዋወቅ በትብብር ለመስራት ይሁንታውን ገለፀ።
በብራዚል የኢትዮጵያ አምባሳደር ልዑልሰገድ ታደሰ ከብራዚል ግዙፉ የቱሪስት አስጎብኚ ድርጅቶች ማህበር ፕሬዝዳንት አና ካሮሊና ሜዲዬሮስ ጋር ተወያይተዋል።
ውይይቱ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ዘርፍ እና በዘርፉ ያሉ መልከ ብዙ ዕድሎች ዙሪያ ላይ ፍሬያማ ምክክር ማድረጋቸውን አምባሳደሩ በማህበራዊ ትስስር አስፍረዋል።
ማኅበሩ በገለጸው ይሁንታም ከኤምባሲው ጋር በመሆን ኢትዮጵያን እንደ ቱሪስት መዳረሻ ለብራዚላዊያን ለማስተዋወቅ በትብብር ለመስራት መስማማታቸውን ገልጸዋል።