ቀጥታ፡

ምክር ቤቱ በመደበኛ ጉባዔው የተለያዩ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል

አዲስ አበባ፤ ጥር 5/2017(ኢዜአ)፡- የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 15ኛ መደበኛ ጉባዔ ነገ ይካሄዳል።

ምክር ቤቱ በጉባዔው የንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ በፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።

በተጨማሪም የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ሁለት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች ላይ ያቀረበውን የስንብት ውሳኔ አስመልክቶ የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ እንደሚያፀድቅ ተገልጿል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሹመትን መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅም ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም