የቤንች የዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል "ቢስት ባር" እየተከበረ ነው

ዣዥ፤ ጥር 5/2017 (ኢዜአ) ፦ የቤንች የዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል የሆነው "ቢስት ባር" በተለያዩ ባህላዊ ኩነቶች እየተከበረ ነው።

በዓሉ በሼይ ቤንች ወረዳ "ዣዥ" በሚሰኘው ታሪካዊ ስፍራ የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው ዛሬ እየተከበረ ያለው።

የቤንች ሸኮ ዞን ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ኮይካ እንዳሉት ቢስት ባር "የመጀመሪያ" ወይም "የበኩር" የሚል ትርጉም አለው።

የዘመን መለወጫ በዓሉ በክረምት ተዘርቶ ከደረሰ የግብርና ምርት በጋራ በመቅመስና በአባቶች ምርቃት የሚከወን በዓል ነው።

በበዓሉ ለደረሰ አዝመራ ለፈጣሪ ምስጋና የሚቀርብበትና ለቀጣዩ ደግሞ ልመና የሚያቀርቡበት፣ የተጣላ በዕርቅ ፍቅር የሚያድስበት የአብሮነት ነጸብራቅ በመሆኑ ትልቅ ቦታ ይሰጠዋል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም