ቀጥታ፡

ማንችስተር ዩናይትድ በኤፍኤ ካፕ አርሰናልን በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈ

አዲስ አበባ፤ ጥር 4/2017 (ኢዜአ) ፦ በእንግሊዝ ኤፍኤካፕ የሶስተኛ ዙር ተጠባቂ መርሃ ግብር ማችስተር ዩናይትድ አርሰናልን በመለያ ምት በማሸነፍ አራተኛውን ዙር ተቀላቅሏል።


ማምሻዉን በኤምሬትስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ብሩኖፈርናንዴዝ በ52ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ማንችስተር ዩናይትድን መሪ አድርጎ ነበር።

ጋብርኤል በ63ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፋት ጎል አርሰናልን አቻ አድርጓል።

የአርሰናል አምበል ማርቲን ኦዴጋርድ በ70ኛው ደቂቃ የተገኘውን የፍጹም ቅጣት ምት ሳይጠቀምበት ቀርቷል።

የማንችስተር ዩናይትዱ ተከላካይ ዲያጎ ዳሎት በ61ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።

ጨዋታው በመደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በአቻ ውጤት በመጠናቀቁ ወደ ጭማሪ ሰዓት አምርቷል።

በጭማሪ ሰዓትም የውጤት ለውጥ ባለመኖሩ ምክንያት አሸናፊውን ለመለየት ቡድኖቹ  ወደ መለያ ምት አምርተዋል።

ማንቸስተር ዩናይትድ በመለያ ምት 5 ለ 3 በማሸነፍ ወደ አራተኛ ዙር ማለፉን አረጋግጧል።

አርሰናል 14 ጊዜ እና ማንችስተር ዩናይትድ 13 ጊዜ የኤፍኤ ካፕ ዋንጫን በማንሳት የውድድሩ ስኬታማ ክለቦች ናቸው።

 

ማንችስተር ዩናይትድ በአራተኛው ዙር ከሌይስተር ሲቲ ጋር ተደልድሏል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም