የፌደራል ፖሊስ የተመሰረተበትን 116ኛ አመት በማስመልከት የተዘጋጀው ስፖርታዊ ውድድር ማጠቃለያ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የፌደራል ፖሊስ የተመሰረተበትን 116ኛ አመት በማስመልከት የተዘጋጀው ስፖርታዊ ውድድር ማጠቃለያ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፤ ጥር 4/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የተመሰረተበትን 116ኛ አመት በማስመልከት ሲካሂድ የቆየው ስፖርታዊ ውድድር የማጠቃለያ ፕሮግራም በአዲስ አበባ ስታዲየም እየተካሄደ ይገኛል።
በመርኃ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ መክዩ መሃመድ እንዲሁም የፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮችና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።
ከታሕሳስ 22 ጀምሮ እስከ ዛሬ ሲካሄድ የቆየው የእግር ኳስ እና የገመድ ጉተታ ውድድር የፍፃሜ ጨዋታዎች በመደረግ ላይ ናቸው።
የወንዶች እግር ኳስ ፍፃሜ በኮሚሽነር ጀነራል ተጠሪ ዋና መምሪያዎች እና በወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ መካከል ይካሄዳል።
በገመድ ጉተታ በወንዶች ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ በሴቶች ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ ከወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ ጋር ይወዳደራሉ።
ላለፋት 12 ቀናት ሲካሄድ በቆየው ውድድር 640 ስፖርተኞች በአምስት የውድድር አይነቶች ተሳትፈዋል።
በመድረኩ በፌደራል ፖሊስ ስትራቴጂክ አመራሮች መካከል የወዳጅነት እግር ኳስ ጨዋታ ተካሄዷል፡፡
በመርኃ ግብሩ ማጠቃለያ የተለያዪ ወታደራዊ ትዕይንቶች ቀርበዋል ፡፡