ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ ስለአፍሪካ ሁሉን አቀፍ የግብርና ልማት ፕሮግራም(ካዳፕ) ምን አለች?

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሁሉን አቀፍ የግብርና ልማት ፕሮግራም(ካዳፕ) አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ለአፍሪካ እና አፍሪካውያን ያላትን መሻት አንጸባርቃለች። በዚህም፦

👉በአፍሪካ ሁሉን አቀፍ የግብርና ልማት ፕሮግራም(ካዳፕ) የተያዙ ግቦች እንዲሳኩ ከአፍሪካ ህብረት እና አባል ሀገራት ጋር በቅርበት እንደምትሰራ፤

👉የአፍሪካ ሁሉን አቀፍ የግብርና ልማት ፕሮግራም(ካዳፕ) ግቦችን የሚያሳኩ የተለያዩ ሀገራዊ ኢኒሼቲቮች እየተገበረች መሆኑን፤

👉የአፍሪካ ሁሉን አቀፍ የግብርና ልማት ፕሮግራም(ካዳፕ) ማዕቀፍ የግብርና ምርታማነትንና የምግብ ዋስትናን ለማሳደግ እንዲሁም ዘላቂነት ላለው የተፈጥሮ ሀብት አጠቀቃም ቁልፍ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ፤

👉የአየር ንብረት ለውጥ፣ የህዝብ እድገት፣ የከተሜነት መስፋፋት እና አሁን ላይ የሚታዩ ዓለም አቀፍ ቀውሶች በግብርናው ዘርፍ ላይ የጋረጠውን ፈተና በውል መገንዘብ እንደሚገባ፤

👉የካዴፕ ግቦችን ለማሳካት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መሪነት የተለያዩ ብሔራዊ ኢኒሼቲቮች እየተገበረች መሆኑን፤

👉በብሔራዊ ስንዴ ኢኒሼቲቭ አማካኝነት ዓመታዊ የስንዴ ምርቷ ወደ 23 ሚሊዮን ቶን ማደጉንና ይህም ሀገሪቱ ለ50 ዓመታት ከውጭ ስታስገባ የቆየውን ስንዴ በራሷ አቅም እንድታመርት እንዳስቻላት፤

👉በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ባለፉት ስድስት ዓመታት ከ40 ቢሊዮን በላይ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች በመተከላቸው የደን ሽፋኑን ከ17 ነጥብ 2 በመቶ ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ ማደጉን፤

👉የሌማት ትሩፋት የእንስሳት ምርታማነትን ማሻሻልና በተለይም የዶሮ፣ የወተት፣ የአሳ፣ የስጋና የማር ምርታማነት እንዲጨምር ማድረጉንና ይህም የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦትን ለማሳደግ አስተዋጽኦ ማበርከቱን፤

👉በአጠቃላይ ኢኒሼቲቮቹ ከምግብ ስርዓት ፍኖተ ካርታ ጋር የተቆራኙ መሆናቸውን፤

👉ግብርና ለአፍሪካ ከዘርፍነት ባለፈ የኢኮኖሚ የጀርባ አጥነት፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ኑሯቸውን የሚመሩበትና ለዘላቂ ልማት ትልቅ አበርክቶ ያለው መሆኑን፤

👉በአፍሪካ የማይበገር እና ዘላቂነት ያለው የግብርናና የምግብ ስርዓት ለመገንባት ለተያዘው ራዕይ ስኬታማነት ኢኖቬሽን፣ አካታችነት እና ዘላቂነት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ፤

👉የግብርና እና የምግብ ስርዓቶችን ለአደጋዎች እና ለፈተናዎች የማይበገር ለማድረግ የአቅርቦት ሰንሰለትን ማጠናከር፣ ብዝሃ የምርት ስርዓትን መፍጠር እና በማህበራዊ ሴፍቲኔት ላይ ሙዓለ ንዋይ በማፍሰስ ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን መደገፍ እንደሚያስፈልግ፤

👉በአፍሪካ ትውልድ ተሻጋሪ የምግብ ዋስትናንና ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ እንዲሁም የበለጸገች አህጉር ለመፍጠር የጋራ ትብብርና ቁርጠኝነት እንደሚያስፈለግ አጽንኦት ሰጥታ አንጸባርቃለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም