ቀጥታ፡

ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ስላሴ ዩጋንዳ ገቡ

አዲስ አበባ፤ ጥር 2/2017(ኢዜአ)፦ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ስላሴ ድህረ ማላቦ የአፍሪካ ሁሉን አቀፍ የግብርና ልማት ፕሮግራም (ካዳፕ) ልዩ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ዛሬ ዩጋንዳ ካምፓላ ገብተዋል።

ፕሬዝዳንቱ ኢንቴቤ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የዩጋንዳ መከላከያ እና አርበኞች ጉዳይ ሚኒስትር ጃኮብ ማርክሰን ኦቦት፣ በዩጋንዳ፣ቡሩንዲ፣ሲሸልስና ኮሞሮስ የኢትዮጵያ አምባሳደር እጸገነት በዛብህ ይመኑ፣ የሃይማኖት አባቶች እና ዲፕሎማቶች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የካዳፕ(Comprehensive Africa Agriculture Development Programme) ልዩ ጉባኤ “በአፍሪካ አስተማማኝ የግብርናና የምግብ ስርዓት መገንባት” በሚል መሪ ሀሳብ በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ በካምፓላ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

ልዩ ጉባኤው ነገ በሀገራት መሪዎች ደረጃ ይከናወናል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም