የባስኬት የምስጋና በዓል "ሾልኣ -ካሻ" ዋዜማ በፓናል ውይይት እየተከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የባስኬት የምስጋና በዓል "ሾልኣ -ካሻ" ዋዜማ በፓናል ውይይት እየተከበረ ነው
ላስካ፤ ጥር 2/2017(ኢዜአ):- የባስኬት የምስጋና በዓል "ሾልኣ- ካሻ" ዋዜማ በፓናል ውይይት በላስካ ከተማ እየተከበረ ነው።
የባስኬቶ ዞን የባህልና ቱሪዝም ዩኒት አስተባባሪ ኃላፊ አቶ ዱባለ ንጉሴ በተለይ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የ"ሾላ-ካሻ" ክብረ በዓል በየዓመቱ የእህል ምርት ከተሰበሰበ በኋላ ይካሄዳል።
የ"ካሻ'' ስርዓትን ባስኬቶዎች ሀገር በቀል ዛፎችን በመንከባከብና ደንን በመጠበቅ የሚከውኑት ሲሆን ክብረ በዓሉም መሰል እሴቶች የሚተዋወቁበት መሆኑንም ገልጸዋል።
በዓሉ በዋናነት አካባቢን መጠበቅ ላይ ትኩረት ስለሚያደርግ ለእርሻ ስራ ተስማሚ የሆነ አየር እንዲኖርና ዓመቱን ሙሉ ዝናብ እንዲዘንብ አስችሏል ብለዋል።
በዓሉ ዛሬ በፓናል ውይይት እየተከበረ መሆኑን ገልፀው በነገው ዕለት በተለያዩ መርሐ ግብሮች እንደሚቀጥልም አመልክተዋል።
መርሃ ግብሩንም ከፌዴራል፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እና ከሌሎች አካባቢዎች የተጋበዙ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና የባህል ተመራማሪዎች እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎች ታድመዋል።