ኢትዮጵያ እና ጣልያን የኢኮኖሚ ትብብራቸውን ማጠናከር በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ እና ጣልያን የኢኮኖሚ ትብብራቸውን ማጠናከር በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ ታኅሣሥ 30/2017(ኢዜአ):- ኢትዮጵያ እና ጣልያን የኢኮኖሚ ትብብራቸውን ማጎልበት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።
በጣልያን የኢትዮጵያ አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ ከጣልያን የውጭ ጉዳዮች እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር ምክትል ዋና ፀሐፊ ጆርጂዮ ሲሊ ጋር ተወያይተዋል።
የሁለትዮሽ ውይይቱ በፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው።
ሁለቱ ወገኖች በውይይታቸው በሀገራቱ ሀገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት እና የኢኮኖሚ ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸው ተገልጿል።
ጆርጂዮ ሲሊ በቅርቡ በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት አድርገው እንደነበር በሮም የኢትዮጵያ ኤምባሲ በመረጃው አመላክቷል።
ኢትዮጵያ እና ጣልያን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን የጀመሩት እ.አ.አ በ1889 መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ።