ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገለጹ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገለጹ
አዲስ አበባ፤ታኅሣሥ 30/2017(ኢዜአ):- ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን በሁለትዮሽና በባለብዝሃ ወገን የትብብር አማራጮች ያላቸውን ግንኙነት ይበልጥ ለማጎልበት እንደሚሰሩ አስታወቁ።
በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማህዲ ከደቡብ ሱዳን የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴንግ አሎር ኩዎል ጋር ተወያይተዋል።
ሁለቱ ወገኖች በውይይታቸው ሀገራቱ ያላቸውን ትስስር ለማሳደግ መስራት እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።
አምባሳደር ነቢል የኢትዮጵያ መንግስት የሁለቱ እህትማማች ሀገራት የጋራ ጉዳዮች በሆኑ መስኮች ላይ ከደቡብ ሱዳን ጋር በቅርበት ለመስራት ቁርጠኛ እንደሆነች መግለጻቸውን በጁባ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።