ሚኒስቴሩ ከዛሬ አመሻሽ ጀምሮ በሥራ ላይ የሚውል የነዳጅ ምርቶች ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ይፋ አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
ሚኒስቴሩ ከዛሬ አመሻሽ ጀምሮ በሥራ ላይ የሚውል የነዳጅ ምርቶች ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፤ ታኅሣሥ 29/2017(ኢዜአ)፦ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከዛሬ አመሻሽ ጀምሮ በሥራ ላይ የሚውል የነዳጅ ምርቶች ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ይፋ አድርጓል።
ሚኒስቴሩ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንደጠቀሰው የነዳጅ ምርቶችን ችርቻሮ ዋጋ መሸጫ በየወሩ እየከለሰ በስራ ላይ እንዲውል በሚኒስቴሮች ምክር ቤት ውሳኔ የተጣለበትን ሃላፊነት አውስቷል።
በዚህም ከዛሬ ታኅሣሥ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት 12 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ የሚደረግ የነዳጅ ምርቶች ችርቻሮ መሸጫ ዋጋን ይፋ አድርጓል።
በዚህም አንድ ሊተር የነዳጅ ምርት ችርቻሮ ዋጋ በብር ሲገበያይ እንደነዳጁ አይነት በሚከተለው መልኩ እንዲሆን መወሰኑን ገልጿል።
አንድ ሊትር ቤንዚን በብር 101.47፣ ናፍጣ በብር 98.98፣ ኬሮሲን በብር 98.98፣ የአውሮፕላን ነዳጅ በብር 109.56፣ የከባድ ጥቁር ናፍጣ በብር 105.97 እንዲሁም የቀላል ጥቁር ናፍጣ በብር108.30 መሆኑን አሳወቋል።