ቀጥታ፡

ታሪካዊ ባላንጣዎቹ ሊቨርፑል እና ማንችስተር ዩናይትድ ነጥብ ተጋርተዋል

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 27/2017 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 20ኛ ሳምንት ተጠባቂ ጨዋታ ሊቨርፑል እና ማንችስተር ዩናይትድ ሁለት አቻ ተለያይተዋል።

ማምሻውን በአንፊልድ ሮድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የ26 ዓመቱ አርጀንቲናዊ ተከላካይ ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ በ52ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ማንችስተር ዩናይትድን መሪ አድርጎ ነበር።

ይሁንና የ25 ዓመቱ ኔዘርላንዳዊ የክንፍ መስመር ተጫዋች በ59ኛው ከመረብ ላይ ያሳረፋት ግብ ሊቨርፑልን አቻ አድርጓል።

የ32 ዓመቱ ግብጻዊ መሐመድ ሳላህ በ70ኛው ደቂቃ የተገኘውን ፍጹም ቅጣት ምት ወደ ግብ በመቀየር ቡድኑን መሪ አድርጓል።

ይሁንና የ22 ዓመቱ ኮትዲቯራዊ አማድ ዲያሎ በ80ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፋት ግብ ማንችስተር ዩናይትድን አቻ አድርጓል።

ሳላህ በሊጉ ያስቆጠራቸውን ግቦች ወደ 18 ከፍ በማድረግ የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን አጠናክሯል።

ውጤቱን ተከትሎ የሊጉ መሪ ሊቨርፑል ነጥቡን ወደ 46 ነጥብ ከፍ አድርጓል።

ማንችስተር ዩናይትድ በ23 ነጥብ ከነበረበት 14ኛ ደረጃ ወደ 13ኛ ከፍ ብሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም