የኢትዮጵያ አየር መንገድ በባሌ ሮቤ ዋቆ ጉቱ አውሮፕላን ማረፊያ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል እያስመረቀ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በባሌ ሮቤ ዋቆ ጉቱ አውሮፕላን ማረፊያ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል እያስመረቀ ነው
ጎባ፤ ታህሳስ 27/2017(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ በባሌ ሮቤ ያስገነባውን የዋቆ ጉቱ አውሮፕላን ማረፊያ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናልን እያስመረቀ ነው።
በምረቃ መርሐ ግብሩ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰውን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራልና የክልሉ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ዋቆ ጉቱ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በሃደ ሲንቄዎችና የአካባቢው መስተዳድር አካላት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።