በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ እና ዱለቻ ወረዳዎች እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ፈንታሌ ወረዳ የርዕደ- መሬት ክስተት የተፈጥሮ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ደውልን ተከተሎ መንግስት የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል - የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን - ኢዜአ አማርኛ
በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ እና ዱለቻ ወረዳዎች እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ፈንታሌ ወረዳ የርዕደ- መሬት ክስተት የተፈጥሮ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ደውልን ተከተሎ መንግስት የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል - የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን

በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ እና ዱለቻ ወረዳዎች እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ፈንታሌ ወረዳ የርዕደ- መሬት ክስተት የተፈጥሮ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ደውልን ተከተሎ መንግስት የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል - የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን
የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በአፋር እና በኦሮሚያ ክልሎች እየተከሰተ ባለው የርዕደ-መሬት ክስተት ሁኔታና ምላሽን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፦
በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ እና ዱለቻ ወረዳዎች እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ፈንታሌ ወረዳ የርዕደ- መሬት ክስተት የተፈጥሮ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ደውልን ተከተሎ መንግስት የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ በእስካሁኑ ሁኔታና ምላሽ እየታየ ያለው ስራ አመርቂ ነው፡፡
በአፋር ክልል ሁለት ወረዳዎች ማለትም አዋሽ ፈንታሌና ዱለቻ(ዱለሳ) ወረዳዎች ለችግሩ ተጋላጭ ናቸው፡፡ በሁለቱም ወረዳዎች ማለትም በአዋሽ ፈንታሌ 6 ተጋላጭ ቀበሌዎች 15,000 ነዋሪዎች ተጋላጭ ሲሆኑ እስከ አሁን 7,000 ወገኖች ከስጋቱ ቀጠና ወደ ሌላ ስፈራ ተጓጉዘዋል፡፡
በዱለቻ ወረዳ ደግሞ 20,000 የሚሆኑ የ2 ቀበሌዎች ወገኖች ተጋላጭ ሲሆኑ፤ ከነዚህ ቀበሌዎች እስከ አሁን 6,223 ህዝብ አካባቢውን ለቀዋል፡፡
በኦሮሚያ ክልል ፈንታሌ ወረዳ የ5 ቀበሌዎች ወገኖች ለአደጋው ተጋላጭ ናቸው፡፡ በ5ቱም ቀበሌዎች 16,182 ሕዝብ ተጋላጭ ሲሆን እስከ አሁን ድረስ 7,350 ሕዝብ ከተጋላጭ ስፍራ ወጥተዋል፡፡ 8,832 የሚሆኑት ቀሪዎቹ ሰዎች ደግሞ በሚቀጥሉት ቀናት ውስጥ ከስፍራው እንዲንቀሳቀሱ እየተሠራ ይገኛል፡፡
ክስተቱን ከአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲና ከሌሎች የሚመለከታቸው ተቋማት የተውጣጡ የሳይንቲፊክ ኮሚቴ፣ ያለውን ሁኔታ እየተከታተለ ሲሆን መገለጽ ያለበትን ቅድመ-ጥንቃቄዎች አስመልክቶ አስፈላጊው መረጃ ለሕዝብ በተከታታይ የሚቀርብ ይሆናል፡፡ ይህንንም ከኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ማህበራዊ ሚዲያዎችና ድህ-ገጽ መከታተል ይቻላል፡፡
የርዕደ መሬት ንዝረቱ ባለበት አካባቢ ያለ ማህበረሰብ ከንዝረቱ በፊት፣ በንዝረቱ ወቅትና ከንዝረቱ በኋላ ያለውን መወሰድ ያለባቸው ጥንቃቄ እንዲወስዱ አስፈላጊው መረጃ እየተሰጠ ይገኛል፡፡
ሰብዓዊ ድጋፍን በተመለከተ እስከ አሁን ለ70,000 የህብረተሰብ ክፍሎች የሚሆን 11,550 ኩንታል ምግብ-ነክ እና ለ7,000 አባወራ የሚሆን ምግብ-ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ወደ ስፍራው ተልኳል፡፡ ይህም በገንዘብ ሲተመን ለምግብ ብር 216,562,500.00 እና ምግብ-ነክ ላልሆኑ ቁሳቁሶች ብር 65,625,000.00 በድምሩ ብር 281,562,500 (ሁለት መቶ ሰማኒያ አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ስልሳ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር) የሚገመት ነው፡፡
በኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በኩል የርዕደ-መሬቱን ባህሪያትና የሚጠይቀውን የጥንቃቄ መልዕክቶች በተከታታይ የምናቀርብ በመሆኑ በተረጋጋና በሰከነ ሁኔታ አደጋውን ለመሻገር ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትኩረትና በንቃት እንዲንቀሳቀሱ እናሳስባለን፡፡
ከኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን
ታህሳስ 26/2017 ዓ/ም
አዲስ አበባ