ቀጥታ፡

የህንዱ ኢንዶገልፍ ክሮፕሳይንስ ኩባንያ በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት እንዳለው ገለፀ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 25/2017(ኢዜአ)፡- የህንዱ ኢንዶገልፍ ክሮፕሳይንስ ኩባንያ በኢትዮጵያ በግብርና ኬሚካልና ማዳበሪያ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት እንዳለው ገልጿል።

በህንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍሰሃ ሻወል ከህንዱ የኢንዶገልፍ ክሮፕሳይንስ ኩባንያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሳንጃይ አጋርዋል ጋር በኢትዮጵያ የግብርና ኬሚካልና ማዳበሪያ ማምረት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም አምባሳደር ፍሰሃ ሻወል በኢትዮጵያ ስላሉ ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮች ለባለሃብቶቹ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በኢትዮጵያ የተተገበረው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እና በፋይናንስ ዘርፉ ለኢንቨስትመንት እየተፈጠሩ ያሉ ምቹ ሁኔታዎች ለባለሃብቶች አማራጭ መሆናቸውን አብራርተዋል።

በኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ እና በአግሮ ኬሚካል ኢንዱስትሪ ያሉትን አዋጭ የኢንቨስትመንት እድሎች ለባለሃብቶቹ አስረድተዋል።

በዚህም በህንድ በአግሮ ኬሚካል እና ማዳበሪያ ምርት ቀደምት የሆነው ኢንዶጎልፍ ክሮፕሳይንስ ኩባንያ በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት እንዳለው አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም