አየር መንገዱ ሶስተኛውን የኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን ተረከበ - ኢዜአ አማርኛ
አየር መንገዱ ሶስተኛውን የኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን ተረከበ
አዲስ አበባ፤ታኅሣሥ 24/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሶስተኛውን የኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን መረከቡን አስታወቀ።
ምቹ እና ዘመናዊ አውሮፕላኖችን ስራ ላይ በማዋል ለደንበኞቻችን ምርጥ አገልግሎት ከመስጠት በተጨማሪ በአቪዬሽን መስኩ በአፍሪካ ስኬታማ የሆንበትን መሪነት እና በዓለም ደረጃ ያለንን ተወዳዳሪነት አጠናክረን እንቀጥላለን ሲል አየር መንገዱ ገልጿል።