የገና በዓል የንግድ ዐውደ ርዕይና ባዛር በባሕር ዳር ሊካሄድ ነው

ባህር ዳር፤ ታኅሣሥ 23/2017(ኢዜአ)፦ "ባዛራችን ለሰላማችን ጥርን በባሕር ዳር" በሚል መሪ ሀሳብ የንግድ ዐውደ ርዕይና ባዛር በባሕር ዳር ከተማ ሊካሄድ መሆኑን ከተማ አስተዳደሩ ገለፀ።

ዐውደ ርዕይና ባዛሩ በባህር ዳር ከተማ በሸማቹና በአምራቹ መካከል ዘላቂ የሆነ የገበያ ትስስር ለመፍጠር ያለመ ነው ተብሏል።

የከተማ አስተዳደሩ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ አደራ ጋሼ እንዳሉት ዐውደ ርዕይና ባዛሩ ከታህሳስ 25 እስከ 28 ቀን 2017 ዓ.ም "ባዛራችን ለሰላማችን ጥርን በባህር ዳር" በሚል መሪ ሃሳብ ይካሄዳል።

ባዛሩ አምራቹና ሸማቹን በቀጥታ በማገናኘት የግብርና፣ የኢንዱስትሪና የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ይገበያዩበታል ብለዋል።

ዐውደ ርዕዩ አምራች ኢንዱስትሪዎችን የማነቃቃት እድል እንዳለ ገልጸው፤ ለዚህም አዘጋጅ ኮሚቴ ተቋቁሞ ሲሰራ መቆየቱን ጠቅሰዋል።

ዐውደ ርዕዩና ባዛሩ በድሮው "አለ በጅምላ" ግቢ ውስጥ እንደሚካሄድ ጠቅሰዋል።

ህብረተሰቡ በስፍራው በመገኘት የሚፈልጋቸውን ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ በቀጥታ ከአምራቾችና ከጅምላ አከፋፋዮች ማግኘት እንደሚችል ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም