ወጣቶች በሀገራዊ ምክክር ሂደት ወሳኝ የመሪነት ሚናቸውን መወጣት አለባቸው - ኮሚሽኑ - ኢዜአ አማርኛ
ወጣቶች በሀገራዊ ምክክር ሂደት ወሳኝ የመሪነት ሚናቸውን መወጣት አለባቸው - ኮሚሽኑ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 23/2017(ኢዜአ)፡- ወጣቶች በሀገራዊ ምክክር ሂደት ወሳኝ የመሪነት ሚናቸውን እንዲወጡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጥሪ አቀረበ።
ኮሚሽኑ ዋይ ቡንቱ ዩዝ ፒስ ቢዩልዲንግ አሊያንስ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከወጣቶች ያሰባሰባቸውን አጀንዳዎች ተረክቧል።
አጀንዳዎቹን የተረከቡት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሉጌታ አጎና ኮሚሽነር አምባዬ ኦጋቶ(ዶ/ር) ናቸው።
ኮሚሽነሮቹ ወጣቶች የጋራ ትርክቶችን በመገንባት ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ገልጸዋል።
ወጣቶች ከሀገራዊ ችግሮቻችን መወጫ ቁልፍ ሚና ላለው የሀገራዊ ምክክር ሂደት ወሳኝ የመሪነት ሚናቸውን እንዲወጡም ጥሪ ማቅረባቸውን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።