ብሔራዊ ቤተ መንግሥት የኢትዮጵያ ትናንት፣ ዛሬና ነገ የተገናኙበት አማካይ ሥፍራ ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ - ኢዜአ አማርኛ
ብሔራዊ ቤተ መንግሥት የኢትዮጵያ ትናንት፣ ዛሬና ነገ የተገናኙበት አማካይ ሥፍራ ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
አዲስ አበባ፤ ታኅሣሥ 22/2017(ኢዜአ)፦ ብሔራዊ ቤተ መንግሥት የኢትዮጵያ ትናንት፣ ዛሬና ነገ የተገናኙበት አማካይ ሥፍራ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ።
ቤተ መንግሥቱ የትናንት ድሎቻችን እና የውጣ ውረድ ታሪካችን መዝገብ፣ የዛሬ የማንሰራራት ዘመናችን መነሻ ወረታችን፣ የነገ ራዕያችንና የመሻታችን ማሳያም ነውም ብለዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው ዕለት ከሚዲያ እና ከቱሪዝም አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ባለሞያዎች ጋር ታሪኩን ጠብቆ በፍጥነት እና በጥራት በታደሰው በዚህ ዕጹብ ድንቅ ሥፍራ ማሳለፋቸውን ገልፀዋል።
በሕዝብና በመንግሥት መካከል መቀራረብ፣ መነጋገር፣ መግባባት እንጂ በግንብ የተከለለ የፖለቲካ ሕይወት አያስፈልግም ብለዋል።
የቤተ መንግሥቱ ለሕዝብ ክፍት መሆንም የዚህ አዲስ የፖለቲካ ዕሳቤ ሁነኛ ትእምርት እንደሆነ ጠቁመዋል።
ብሔራዊ ቤተ መንግሥት የኢትዮጵያን ዘመናዊ የመንግሥትነት ታሪክ ለዛሬውና ለነገው ትውልድ ገልጠው ከሚያሳዩ እና ከሚያስተምሩ ውድ ቅርስና ሀብቶቻችን አንዱ ነው ብለዋል።
ቤተ መንግሥቱ የትናንት ድሎቻችን እና የውጣ ውረድ ታሪካችን መዝገብ፣ የዛሬ የማንሰራራት ዘመናችን መነሻ ወረታችን፣ የነገ ራዕያችንና የመሻታችን ማሳያም ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ገልጸዋል።