ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ የመጀመሪያ ስብሰባውን አካሄደ

አዲስ አበባ፤ ታኅሳስ 22/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ የመጀመሪያ ስብሰባውን ታኅሳስ 22 ቀን 2017 አካሂዷል።

ባንኩ በማቋቋሚያ አዋጁ በተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መሰረት የተቋቋመው የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ከባንኩ ዋጋን ከማረጋጋት ቀዳሚ ዓላማ ጋር የተጣጣሙ የገንዘብ ፖሊሲ ምክረ ሀሳቦችን ለባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ያቀርባል፤ ያጸድቃል።

በዚህ ረገድ ኮሚቴው የኢትዮጵያን የዋጋ ግሽበት፣ የፊስካል፣ የውጭ ኢኮኖሚ፣ የገንዘብ አቅርቦት እና የፋይናንስ ዘርፍ አዝማሚያዎችን አጠቃላይ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ አመልካቾችን እንዲሁም በሀገር ውስጥ የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታዎች ላይ ጉልህ አንደምታ ያላቸውን ዓለም አቀፍ ሁኔታዎችን ይገመግማል።

ኮሚቴው ከእነዚህ ማክሮ ኢኮኖሚያዊ ግምገማዎችና ከቅርብ ጊዜ የወደፊት እይታዎች አጠቃላይ ግምገማ በመነሣት በገንዘብ ፖሊሲው ተግባራዊ
የሚደረጉ ተገቢ ናቸው ብሎ ያመነባቸውን ዝርዝር የፖሊሲ እርምጃዎች በተመለከተ ምክረ ሐሳብ ያቀርባል።

በዚሁ መሠረት ኮሚቴው በቅርብ ጊዜ በተከሰቱ የሀገሪቱ የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታዎች ላይ የተወያየ ሲሆን፤ በውይይቱ ያካተታቸው ጉዳዮች የሚከተሉት ናቸው፡-


 


 


 

 


 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም