ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ በፊፋ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈች

አዲስ አበባ ፤ ታህሳስ 22/2017(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በዘጠነኛው የፊፋ ከ17 ዓመት ሴቶች ዓለም ዋንጫ የአፍሪካ ዞን ማጣሪያ በፎርፌ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል።

ኢትዮጵያ በሞሮኮ አስተናጋጅነት በ2018 ዓ.ም በሚካሄደው ውድድር የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዋን ከዚምባቡዌ ጋር በጥር ወር 2017 ዓ.ም ለማድረግ መርሃ ግብር ወጥቶላት ነበር።

ይሁንና ዚምባቡዌ ራሷን ከማጣሪያው ራሷን ማግሏን ተከትሎ ኢትዮጵያ በፎርፌ ውጤት ወደ ሁለተኛው ዙር ማለፏን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

ኢትዮጵያ በቀጣይ ዙር የግብፅ እና ካሜሩን አሸናፊን እንደምትገጥም ገልጿል።

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ራውዳ አሊ ትናንት ለማጣሪያው ጨዋታ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገው እንደነበር አይዘነጋም።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም