ቀጥታ፡

የመጀመሪያው የብስክሌት ፌስቲቫል በመዲናዋ ሊካሂድ ነው

አዲስ አበባ፤ ታኅሣሥ 21/2017(ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ የብስክሌት ፌስቲቫል ሊያካሂድ መሆኑን የከተማዋ ትራንስፖርት ቢሮ ገለፀ፡፡

የቢሮው ሃላፊ አቶ ያብባል አዲስ እንዳሉት ፌስቲቫሉ የፊታችን ታኅሣሥ 27 ቀን 2017 ዓ.ም ”ብስክሌት በአዲስ” በሚል መሪ ሃሳብ ከአደዋ ድል መታሰቢያ እስከ ራስ መኮንን ድልድይ ድረስ ይካሄዳል።

ፌስቲቫሉ በየወሩ በተመረጡ የመዲናዋ መንገዶች በቀጣይነት ይደረጋልም ብለዋል።

የከተማዋን ትራንስፖርት ምቹ፣ አስተማማኝ እና ተደራሽ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅሰው፤ ፌስቲቫሉ ህብረተሰቡ ለሞተር አልባ ትራንስፖርት ግንዛቤን ለማሳደግ ያለመ ነው ብለዋል።፡

በተለይም የመዲናዋ ኮሪደር ልማት ብስክሌትን ጨምሮ ለሞተር አልባ ትራንስፖርት መስፋፋት ምቹ ሁኔታን መፍጠሩን ገልጸዋል።

የብስክሌት ትራንስፖርት ከጤና፣ ከትራፊክ ደህንነት፣ ከከባቢ አየር ጥበቃ፣ ከጊዜ አጠቃቀም አንጻር ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም