ቀጥታ፡

አሰልጣኝ ራውዳ አሊ ለፊፋ ከ17 ዓመት ሴቶች ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል 

አዲስ አበባ ፤ ታህሳስ 21/2017(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ራውዳ አሊ ቡድኑ በዘጠነኛው የፊፋ ከ17 ዓመት ሴቶች ዓለም ዋንጫ የአፍሪካ ዞን ማጣሪያ ከዚምባቡዌ ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል።

የዓለም ዋንጫ ውድድሩ በ2018 ዓ.ም በሞሮኮ አስተናጋጅነት ይካሄዳል።

በውድድሩ ላይ ከስድስት አህጉራት የእግር ኳስ ኮንፌዴሬሽኖች የተወጣጡ 24 አገራት ይሳተፋሉ።

አፍሪካ ከአዘጋጇ ሞሮኮ በተጨማሪ አራት አገራት የማሳተፍ ኮታ አላት። 

በማጣሪያው ላይ የምትሳተፈው ኢትዮጵያ በመጀመሪያው ዙር ከዚምባቤዌ ጋር በጥር ወር 2017 ዓ.ም ጨዋታዋን ታደርጋለች።

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ራውዳ አሊ ለማጣሪያ ጨዋታው ለ23 ተጫዋቾች ዛሬ ጥሪ ማድረጋቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ነገ ልምምዳቸውን እንደሚጀምሩም ገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም