ቀጥታ፡

ምሁራን ለዘላቂ ሰላምና ለሀገር ግንባታ ያላቸውን ሚና የተመለከተ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 21/2017(ኢዜአ)፡- ምሁራን በዘላቂ ሰላምና ሀገር ግንባታ ሂደት ላይ ያላቸውን ሚና የተመለከተ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

የሰላም ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ውይይት “የልሂቃን ሚና ለዘላቂ ሰላምና ለሀገር ግንባታ” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።


 

በመድረኩ ላይ የሰላም ሚኒስቴር አመራሮች፣ የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ተወካዮች፣ የታሪክ ምሁራን፣ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የሲቪክ ማህበራት ተወካዮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ መሆናቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የውይይቱ አላማ ምሁራን ዘላቂ ሰላም በመገንባት፣ ብሔራዊ መግባባት በማጎልበት እና በሀገር ግንባታ ሂደት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ማስቻል መሆኑም በመረጃው ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም