ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ የከፍታ መታያ - የኢትዮጵያ አየር መንገድ


👉 የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ መዳረሻዎቹን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሰፋ የሚገኝ፤

👉 በላቀ የአቪዬሽን ስልጠና ግንባር ቀደም ውጤት እያስመዘገበ ያለ፤

👉 የአዳዲስ እና ዘመናዊ አውሮፕላኖች ባለቤት ለመሆን ሁሌም የሚተጋ፤

👉 ለኢትዮጵያ እና ለአፍሪካ አቪዬሽን ዕድገት የራሱን ጉልህ አስተዋፅዖ እያበረከተ የሚገኝ፤

👉 የአፍሪካ ሀገራት አየር መንገዶችን በማቋቋም እና በማስተዳደር የአፍሪካ ኩራትነቱን በተግባር እያስመሰከረ ያለ፤

👉 ለቱሪዝም ኢንደስትሪው ልማትና ዕድገት የራሱን አሻራ እያኖረ ያለ፤

👉 ለደንበኞቹ ምቾት የሚጨነቅ የኢትዮጵያዊ እንክብካቤ እና መስተንግዶ ማሳያ፤

👉 በዘመናዊ እና ቀልጣፋ የበረራ አገልግሎቱ በየዓመቱ ትልልቅ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን የሚቀዳጅ፤

👉 በምቹ እና ዘመናዊ አውሮፕላኖች በልዩ ኢትዮጵያዊ መስተንግዶ የሚያገለግል፤

👉 ከደመናው በላይ የሚቀዝፍ የኢትዮጵያ የከፍታ መታያ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኢትዮጵያ ብሎም የአፍሪካ ኩራት፤

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም