ቀጥታ፡

የማዕከሉ ስልጠና የተሟላ ፖሊሳዊ ብቃትና ስብዕና ለመላበስ ቁልፍ ሚና ይጫወታል-ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል

አዲስ አበባ፤ታህሳስ 18/2017 (ኢዜአ)፦በጅግጅጋ የፖሊስ ማሰልጠኛ ማዕከል እየተሰጠ ያለው ስልጠና የተሟላ ፖሊሳዊ ብቃትና ስብዕና ለመላበስ አይተኬ ሚና እንደሚጫወት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ገለጹ።

ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ፥ በማዕከሉ የ25ኛ ዙር ምልምል ሰልጣኞችንና የስልጠናውን ሂደት ጎብኝተዋል።


 

ኮሚሽነር ጀነራሉ፥ በስልጠና ማዕከሉ እየተሰጠ ያለው ትምህርት እና ስልጠና ሰልጣኞች በሥራ ላይ ሲሰማሩ የተሟላ ፖሊሳዊ ብቃትና ስብዕና ላይ ለመገኘት ወሳኝ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።

እስከ አሁን ባለው የስልጠና አሰጣጥ ሂደትና በሰልጣኞች የትምህርት አቀባበልና ብቃት ደስተኛ እንደሆኑ መናገራቸውን ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም