የኢትዮጵያ ዋንጫ ሁለተኛ ዙር መርሃ ግብር ነገ ይጀመራል - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ዋንጫ ሁለተኛ ዙር መርሃ ግብር ነገ ይጀመራል
አዲስ አበባ፤ ታኅሣሥ 17/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ዋንጫ ሁለተኛ ዙር ጨዋታዎች ከነገ ጀምሮ በአበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም እና ሀዋሳ አርቴፊሻል ሜዳ እንደሚካሄዱ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።
መርሃ ግብሩ እስከ ታህሳስ 21 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚቆይ አመልክቷል።
አምና በፍፃሜ ጨዋታ የተከሰተው የስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል ዘንድሮም እንዳይደገም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይቶች እየተደረጉ እንደሚገኝ ተገልጿል።
በዚህም መሠረት በጉዳዩ ላይ ዘላቂ መፍትሄ እስኪገኝ ድረስ በሁለተኛው ዙር የሚደረጉ ጨዋታዎች ያለ ተመልካች በዝግ እንዲከናወኑ ውሳኔ መተላለፉን የፌዴሬሽኑ መረጃ ያመለክታል።