ነገሌ ቦረና ጠቅላላ ሆስፒታል የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገለት - ኢዜአ አማርኛ
ነገሌ ቦረና ጠቅላላ ሆስፒታል የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገለት
ነገሌ ቦረና፤ ታህሳስ 17/2017(ኢዜአ)፡- የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግሥታት ባለስልጣን(ኢጋድ) ለነገሌ ቦረና ጠቅላላ ሆስፒታል 20 ሚሊዮን ብር የሚገመት የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።
ድጋፉ የተገኘው በኢጋድ ዋና ፀሐፊ በወርቅነህ ገበየሁ(ዶ/ር) አማካኝነት ሂውማን ብሪጅ ከተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት እንደሆነም ተመልክቷል።
በድጋፍ መርሃ-ግብሩ ላይ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግስታት ባለስልጣን የኢትዮጵያ ተጠሪ አቶ አበባው ቢሆነኝ፣ የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብዱርቃድር ገልገሎ፣ የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ቦኮና ጉታ እንዲሁም የምስራቅ ቦረና ዞን የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።
የተደረገው ድጋፍ የሆስፒታል አልጋዎች፣ የአካል መደገፊያ መሳሪያዎች፣ የላቦራቶሪ መሳሪያዎችና ሌሎች ቁሳቁሶች እንደሚገኙበት ተመላክቷል።
ድጋፉ የሆስፒታሉን አገልግሎት የሚያሳድግ መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን፤ ሆስፒታሉ በምሥራቅ ቦረናና አካባቢው ለሚገኙ 100 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ነዋሪዎች አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ተገልጿል።