ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ እና ተርኪዬ በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ታህሳስ 16 /2017 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ እና ተርኪዬ በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል።

በተርኪዬ የኢትዮጵያ አምባሳደር አደም መሐመድ ከተርኪዬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የምስራቅ እና ሰሜን አፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ኤሊፍ ኮሞግሉ ጋር መክረዋል።

ውይይቱ የጋራ ፍላጎታቸው በሆኑ የሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑን በአንካራ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም