የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ በዲላ ከተማ አቀባበል ተደረገለት - ኢዜአ አማርኛ
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ በዲላ ከተማ አቀባበል ተደረገለት
ዲላ፤ታህሳስ 16/2017 (ኢዜአ):- የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ በጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ አቀባበል ተደረገለት።
ዋንጫው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚኖረውን ቆይታ ዛሬ በጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ መጀመሩ ተመላክቷል።
የጌዴኦ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ሃላፊ ወይዘሮ ዜና ማሞ ለኢዜአ እንደገለጹት ዋንጫው በዞኑ ለአንድ ወር ቆይታ ያደርጋል ።
ዋንጫው በዞኑ በሚኖረው ቆይታ ከ120 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱን ተናግረዋል ።
ህብረተሰቡ በቦንድ ግዥ በመሳተፍ ግድቡን ለማጠናቀቅ ድጋፉን እንዲያጠናክር ጠይቀዋል።
ዋንጫው ወደ ዞኑ ሲገባ ደማቅ አቀባበል የተደረገለት ሲሆን በስነ ስርአቱ ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ገብረመስቀል ጫላን ጨምሮ ሌሎች የፌደራልና የክልል እንዲሁም የዞን የስራ ሃላፊዎች አባገዳዎችና ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።