ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ የቻን የማጣሪያ የመልስ ጨዋታዋን ከሱዳን ጋር ታደርጋለች 

አዲስ አበባ፤ታህሳስ 16 /2017 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሀገራት ሻምፒዮና (ቻን) ማጣሪያ የመልስ ጨዋታዋን ዛሬ ከሱዳን ጋር ታካሂዳለች።

የሁለቱ አገራት ጨዋታ ከቀኑ 11 ሰዓት በሊቢያ ቤንጋዚ በሚገኘው ማርታያርስ ኦፍ ፌብሩዋሪ ስታዲየም ይካሄዳል።

ብሔራዊ ቡድኖቹ ታህሳስ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ባደረጉት የመጀመሪያ ጨዋታ ሱዳን 2 ለ 0 አሸንፋለች።

በጊዜያዊ አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለመልስ ጨዋታው የመጨረሻ ልምምዱን ጨዋታው በሚደረግበት ስታዲየም ትናንት አከናውኗል። 


 

ኢትዮጵያ ወደ ቻን ውድድር ለማለፍ ሱዳንን ሶስት እና ከዚያ በላይ በሆነ የግብ ልዩነት ማሸነፍ ይጠበቅባታል።

ቡድኑ ከዚህ ቀደም በውድድሩ የሶስት ጊዜ ተሳትፎ አድርጓል።

ስምንተኛው የቻን ውድድር ከጥር 24 እስከ የካቲት 21 ቀን 2017 ዓ.ም በኬንያ፣ ታንዛንያ እና ዩጋንዳ ጣምራ አዘጋጅነት ይካሄዳል።


 

በቻን ውድድር አዘጋጆቹን ጨምሮ 19 አገራት ይሳተፋሉ።

በውድድሩ ላይ የሚሳተፉ አገራት እስከ ሳምንቱ መጨረሻ ቀናት በሚደረጉ የመልስ ጨዋታዎች ይለያሉ።

የአፍሪካ አገራት ዋንጫ (ቻን) የአገር ውስጥ ሊግ ተጫዋቾች ብቻ የሚሳተፉበት ውድድር ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም