ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለፈረንጆች የገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለፈረንጆች የገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፤ ታኅሳስ 16 /2017(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለፈረንጆች የገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመላው ዓለም በዓሉን ለሚያከብሩ በሙሉ፣ ለኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ወዳጆች፣ የዳያስፖራ ማኅበረሰብ እና የዓለም ቤተሰብ መልካም የገና በዓል እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ ሲሉ በኤክስ ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል።
የበዓል ወቅቱ የደስታ፣ የሰላም እና የአንድነት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።