የሰላም ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን በአገራዊ የሰላም ግንባታ ስራዎች ዙሪያ በጋራ እንደሚሰሩ ገለፁ - ኢዜአ አማርኛ
የሰላም ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን በአገራዊ የሰላም ግንባታ ስራዎች ዙሪያ በጋራ እንደሚሰሩ ገለፁ
አዲስ አበባ፤ ታኅሣሥ 15/2917(ኢዜአ)፦ የሰላም ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን በአገራዊ የሰላም ግንባታ ስራዎች ዙሪያ በጋራ እንደሚሰሩ ገለፁ።
የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትሩ አቶ መሀመድ እድሪስ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጋር ትውውቅ አድርገዋል።
በዚሁ ወቅትም በኢትዮጵያ የተጀመረውን ሰላም አጠናክሮ ለመቀጠል በሚችልበት ሁኔታ የጋራ ምክክር አድርገዋል።
ቤተ-ክርስቲያኗ ከመንግስት ጋር በመደጋገፍና በመቀራረብ በሰላም ዙሪያ ከመቼውም በላይ በትጋትና በመቀራረብ እንደምትስራ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ አረጋግጠዋል።
የሰላም ሚኒስትሩ ለትውውቅና ለውይይት ወደ መንበረ ፓትሪያርክ በመምጣታቸውም አድንቀዋል።
ሚኒስትሩ አቶ መሀመድ እድሪስ በበኩላቸው ቤተ-ክርስቲያኗ በሰላምና በሀገረ መንግስት ግንባታ ካላት የካበተና የዳበረ ልምድ በመነሳት የተጀመረው የሰላም ሂደት እንዲጎለብት እና የሰላም ፈተናዎች በዘላቂነት መፍትሄ እንዲመጣ የበኩሏን ሚና ትወጣ ዘንድ ጠይቀዋል።
መንግስት ሁልጊዜም ለሰላም የሚከፈል ዋጋን ለመክፍል ያለውን ቁርጠኝነትም ገልጸዋል።
ለዚህ ደግሞ የሰላም ሚኒስቴር ከሁሉም ሃይማኖት ተቋማት እና አባቶች ጋር በትብብርና በቅርበት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል፡፡