በሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የወጣው መግለጫ ከሃቅ የራቀ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የወጣው መግለጫ ከሃቅ የራቀ ነው
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 15/2017(ኢዜአ)፦የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዶሎ ከተማ ለተፈጠረው ግጭት የኢትዮጵያ ኃይሎችን ወንጅሎ ያወጣው መግለጫ ከሀቅ የራቀ ነው።
ሀሰተኛ ውንጀላው በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማስተካከል የተጀመረውን ጥረት ለማደናቀፍ ያለመ መሆኑንም የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።
ውንጀላው የአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ዘላቂ ሠላምና መረጋጋት እንዳይሰፍን የሚሹ የሦስተኛ ወገን አካላት ድርጊት ነው።
በአንካራ ስምምነት ላይ እንደተገለጸው ሁለቱ ሀገራት የሠላም ቁርጠኝነት እንዳይደናቀፍ ክፍተት ሊፈጥሩም አይገባም።
የኢትዮጵያ መንግሥት ከሶማሊያ ፌዴራል መንግሥትና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን መሰል አደጋዎችን ለመከላከል ተባብሮ ይሰራል።
ኢትዮጵያ በአንካራ ስምምነት መሰረት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማደስ እና ለማጠናከር ያላትን ቁርጠኝነት አጠናክራ ትቀጥላለች።
የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ለሠላም መስፈን ያላቸውን ቁርጠኝነት ከሁለትዮሽ አጋርነት ባለፈ ቀጣናዊ ትብብርን አጠናክሮ የሚያስቀጥልም ነው።