ቀጥታ ስርጭት

በኦሮሚያ ክልል ማያ ከተማ አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ስራዎች በመከናወን ላይ ናቸው

ማያ፤ ታህሳስ 15/2017(ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል ማያ ከተማ አስተዳደር በመከናወን ላይ ያሉ የልማት ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ መሆናቸውን የጨፌ ኦሮሚያ ምክትል አፈ ጉባዔ አቶ ኤሊያስ ኡመታ ገለጹ።

ምክትል አፈ ጉባዔው እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በማያ ከተማ አስተዳደር የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ስራዎችን እየገመገሙ ነው።

በእለቱም በከተማ አስተዳደሩ በበጀት ዓመቱ ሁለተኛ ሩብ ዓመት በፓርቲና በመንግስት የተከናወኑ ስራዎች ሪፖርት ቀርበዋል።


 

በመድረኩም ምክትል አፈ ጉባዔው አቶ ኤሊያስ በአካባቢው የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚከናወኑ ስራዎች ምልከታ እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የሚከናወኑ ስራዎችም የህዝቡን ጥያቄ የሚመልሱና የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት በተግባር የሚያረጋግጡ መሆን ይገባቸዋል ብለዋል።

በተለይም የከተማውን ነዋሪዎችና በአስተዳደሩ ሥር የሚገኙ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ለማድረግ በተለያዩ ኢኒሼቲቮች እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ገልጸው፤ ይህን ማጎልበት ይገባል ብለዋል።

በግምገማ መድረኩ የማያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኢፍራህ ወዚር(ዶ/ር) እና ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ የፓርቲና የመንግስት የስራ ሃላፊዎች የተገኙ ሲሆን የተከናወኑ ስራዎች የመስክ ጉብኝት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም